image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ ተጋራ

ታህሳስ 27, 2017
በክ/ከተማው ምንም የገቢ ምንጭ ለሌላቸው፣ ለማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ ፣ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው እና አቅመ ደካማ ወገኖች የማዕድ ማጋራት መርሐ-ግብር ተካሂዷል። የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ በማዕድ ማጋራቱ ባደረጉት ንግግር እንደገለፁት መንግስት ዘላቂ የልማት ፕሮግራምን በመተግበር የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር በቋሚነት ለማቃለል እየሰራ ይገኛል ብለው ነገር ግን ችግሩ ካለው ስፋት አንፃር ማዕድ እያጋራን አንድነታችንን እያጠናከርን ችግሮችን በጊዚያዊነት የማቃለል ስራ እያከናወን እንቀጥላለን በማለት ተናግረዋል። በጎ ስናደርግ አረጋዊያንን ስንደግፍ የምናተርፈው ብዙ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በጎ ፈቃደኛ ባለሀብቶችን በማስተባበር አረጋዊያን በዓሉን ተደስተው እንዲውሉ ለማድረግ ድጋፋችንን ሳይቆራረጥ ይቀጥላል በማለት ገልፀዋል። በአንድ በኩል ዘላቂ ልማትን እየተገበርን በሌላ በኩል ደግሞ አብሮነታችንን በማጠናከር በማዕድ ማጋራት የዜጎችን ማህበራዊ ችግሮች እያቃለልን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል። የልደታ ክ/ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንግዳው ጓዴ እንደተናገሩት አቅመ ደካሞች በዓልን ተደስተው እንዲውሉ የሚያስችል ማዕድ የምናጋራበት በዓል አዳብረናል ብለው ተግባሩ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል በማለት ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች